

ታሪካችን
አሰገደች አስፋው አረጋውያን መርጃ እና መልሶ ማቋቋሚያ ድርጅት በ1983 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ የተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ የበጎ አድራጎት ተቋም ነው፡፡ ድርጀቱን የመሰረቱት ወይዘሮ አሰገደች ጎዳና የወጡ አዛውንትን ለመታደግ በማሰብ በግል የመኖሪያ ቤታቸው 6 አዛውንትን የመጠለያ፣ የአልባሳት እና የምግብ አገልግሎት በመስጠት ነው የጀመሩት፡፡
ይህ ጅማሮ እና የተረጂ አዛውንት ቁጥር መጨመር የወ/ሮ አሰገደች ወዳጆችን እና ልጆችን በበጎ አድራጎቱ ጥረት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ አስገደዳቸው፡፡ የኋላ ኋላ እንቅስቃሴው የመንግስትንም ድጋፍ በማግኘቱ፣ መንግስት ማእከሉ አሁን የሚገኝበትን መሬት በመስጠት እና የእርዳታው እንቅስቃሴ የበጎ አድራጎት ድርጅት ህልውና እንዲኖረው በማድረግ የበጎ አድራጎት ሂደቱ አድማሱን እንዲያሰፋ የበኩሉን አሰተዋጽዎ አበርክቷል፡፡
በአሁኑ ወቅት በአሰገደች አስፋው አረጋውያን መርጃ እና መልሶ ማቋቋሚያ ድርጅት 110 አዛውንት የተሟላ ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡
እንተዋወቅ
ድርጅቱን ያቋቋሙት እና አሁን ያለበት ደረጃ ለይ እንዲደርሰ ከፍተኛ ጥረት ያደረጉት ወ/ሮ አሰገደች እና ቤተሰባቸው በከፊል፡፡

ወ/ሮ አሰገደች አሰፋው

ወ/ሮ ኤልሳ ብሩ

ወ/ሮ እመቤት አሸኔ
ምን ያስባሉ
አዛውንትን ለመርዳት እና ለማቋቋም በጀመርነው ጥረት ላይ ማሳተፍ ይፈልጋሉ? ሊያካፍሉን የሚወዱት ሃሳብ አልዎት? በዚህ በጎ አድራጎት ላይ አስተዋፅዎ ማድረግ ይፈልጋሉ?