መጠለያና አልባሳት

በማእከሉ ውስጥ በአሁኑ ወቅት 91 አዛውንት (66 ወንድ እና 25 ሴት) ሙሉ የመጠለያ እና የአልባሳት እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡   ከዚህ በተጨማሪም የግል ንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች አቅርቦት በተሟላ ሁኔታ ያገኛሉ፡፡ ተጠቃሚ ከሆኑት አዛውንት መሃከል 6 አይነ ስውራን እና 5 አካል ጉዳተኞች ይገኙበታል፡፡

የምግብ አቅረቦት

በምግብ አቅርቦት በኩል በማእከሉ ውስጥ ለሚኖሩ 91 አዛውንት (66 ወንድ እና ሃያ አምስት ሴት) እና ከማእከሉ ውጪ ላሉ 20 አዛውንት (17 ወንድ እና 3 ሴት) ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ይቀርባል፡፡ የምግብ አቅርቦቱ የአዛውንቱን የጤና ሁኔታ ያገናዘበ ነው፡፡ ስኳር እና ደም ግፊት ላለባቸው አዛውንት ከስንዴ እና ጨው ነፃ ምግቦች ይሰናዳሉ ፡፡

የህክምና እርዳታ

ማእከሉ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ድሬዳዋ ቅርንጫፍ፣ ከድል ጮራ ሆሰፒታል፣ እና ከማዘር ትሬዛ ሚሽነሪዎች ቻሪቲ ጋር ባደረገው ቅንጅት በተዘጋጁ የህክምና ፕሮግራሞች 91 አዛውንት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በማእከሉ አንድ የህክምና ክሊኒክ ለማቋቋም ስራዎች ተጀምረዋል፡፡

ፊዚዮቴራፒ እና ሴራጂም

የኢፌዲሪ አገር መከላከያ ሰራዊት ለማእከሉ በሰጠው የስልጠና ጥሪ በማእከሉ የሚሰሩ ነርሶች የፊዚዮቴራፒ እና ሴራጂም ስልጠና ወስደው በማእከሉ ለሚገኙ አዛውንት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ በአጥንት እና ተጓዳኝ ችግሮች የተጎዱ አዛውንት ከዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

የገንዘብ እርዳታ

የገንዘብ እረዳታው ፕሮግራም 20 (1 ወንድ እና 19 ሴት) አዛውንትን ተጠቃሚ ያደረገ ፕሮግራም ነው፡፡ በዚህ ፕሮግራም የሚረዱት የራሳቸው መጠለያ ያላቸው ሆነው የእለት ጉርሳቸውን ማሟላት ያልቻሉ አዛውንት ናቸው፡፡

ገቢ ማመንጫዎች

የከብት ርቢ

የከብት ርቢው ቋሚ የወተት ምርት የሚያስገኝ ሲሆን ይህ ምርት በማእከሉ የሚገኙ አዛውንትን የወተት ምርቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማድረጉም በላይ ለሽያጭ ውሎ ገቢ እያመነጨ ይገኛል፡፡

የአትክልት እና ፍራፍሬ እርሻ

የፍራፍሬ እርሻው  የብርቱካን፣ የሎሚ፣ ኮመጣጤ እና ቃሪያ ምርት ይሰጣል፡፡ ይህ ምርት ገበያ ላይ ውሎ ለድረጅቱ ገቢ ያመነጫል፡፡ የብርቱካን ምርት ወቅት ላይ ለአዛውንቱም ከምግባችው ጋር ብርቱካን ይቀርብላቸዋል፡፡

ምን ያስባሉ

አዛውንትን ለመርዳት እና ለማቋቋም በጀመርነው ጥረት ላይ ማሳተፍ ይፈልጋሉ? ሊያካፍሉን የሚወዱት ሃሳብ አልዎት? በዚህ በጎ አድራጎት ላይ አስተዋፅዎ ማድረግ ይፈልጋሉ?